የቴሌግራም ቻናልዎን ወደ እውነተኛ ሱቅ ይቀይሩት።
ተከታዮችዎ ፖስቶችዎን ሁልጊዜ ያነባሉ። ሸጋ ሾፕ ያንን ቻናል እቃዎችን መፈለጊያ፣ ዘንቢል፣ ለየብቻ ቻት ማድረጊያ፣ ትዕዛዝ መከታተያ እና ራሱን የሚያረጋግጥ የክፍያ ስርዓት ወዳለው እውነተኛ ሱቅ ይቀይረዋል።
ቻናል የፖስቶች ማሳያ ነው። ሱቅ ግን እውነተኛ መገበያያ ነው።
በተለመደው የቴሌግራም ቻናል ላይ፣ ገዢዎች ፖስቶችን እያሸበለሉ ለማዘዝ የውስጥ መስመር (DM) ይጽፉልዎታል። ምንም የተቀነባበረ ወይም ክትትል የሚደረግበት ነገር የለም። ሸጋ ሾፕ ያንኑ ቻናል ወደ እውነተኛ ሱቅ ይቀይረዋል።
የተለመደው ቻናል
የእርስዎ ሸጋ ሾፕ
ሱቅ የሚያስብሉት ስድስት ዋና ዋና ነገሮች
ባዮ ላይ የሚቀመጥ ሊንክ ወይም ተራ ቦት አይደለም። የሸጋ ሾፕ ዋና አላማ 'ፖስቶቼን እዩልኝ' ከሚለው ወደ 'ሱቄን ጎብኙልኝ' የሚያሸጋግር መድረክ መፍጠር ነው።
ቻናልዎ ወደ እውነተኛ ሱቅ ይቀየራል
ፖስት የሚያደርጉት እያንዳንዱ እቃ በቀላሉ ለመጎብኘት ምቹ ወደሆነ ሱቅ ይገባል — ገዢዎች ይፈልጋሉ፣ በምድብ ያጣራሉ፣ እንዲሁም ፖስቶችን እያሸበለሉ እያንዳንዷን እቃ በውስጥ መስመር ከሚጠይቁዎት ይልቅ በርካታ እቃዎችን በአንድ ዘንቢል ውስጥ ይጨምራሉ።
ከሰው-ወደ-ሰው ቻት፣ ለእያንዳንዱ እቃ
የገዢዎች ጥያቄ ልክ ከጠየቁት እቃ ጋር የተገናኘ የግል የቻት መስኮት ይከፍታል — 'ይሄ እቃ አለ?' የሚለው ጥያቄ የትኛውን እቃ እንደሆነ መገመት አያስፈልግም።
የራስዎ የሱቅ አድራሻ
እያንዳንዱ ሱቅ ነፃ yourshop.shegashop.com አድራሻ ያገኛል — አንድን ሊንክ በፈለጉት ቦታ ያጋሩ። ስራዎ ሲያድግ ደግሞ የራስዎን ዶሜይን (domain) መጠቀም ይችላሉ።
የትዕዛዝ ክትትል፣ ከጅምሩ እስከ ርክክቡ
በመጠባበቅ ላይ፣ ተረጋግጧል፣ ተልኳል፣ ደርሷል — እያንዳንዱ ትዕዛዝ የማድረሻ አድራሻ ይኖረዋል፤ ትዕዛዝ ሲገባም ወዲያውኑ መልዕክት ይደርስዎታም።
ራሳቸውን የሚያረጋግጡ ክፍያዎች
የባንክ ዝውውር ደረሰኞች በሰከንዶች ውስጥ በራሳቸው ይረጋገጣሉ — የገንዘቡ መጠን፣ ላኪው፣ ማጣቀሻው፣ እንዲሁም ድግግሞሽ መኖሩ ይጣራል። ከዚህ በኋላ ስክሪንሾቶችን አፍጥጦ ማየት አያስፈልግም።
ወደ ቻናልዎ ፖስት ያድርጉ እና መርሐግብር ያስይዙ
እቃዎችን ወይም አጭር ቪዲዮን ከነ መግዣ ቁልፉ ወደ ቻናልዎ ይላኩ — አሁኑኑ ፖስት ያድርጉ ወይም እርስዎ ኦንላይን በማይሆኑበት ጊዜ ራሳቸው ፖስት እንዲሆኑ መርሐግብር ያስይዙላቸው።
ስምንት ተጨማሪ ተግባራት፣ በጸጥታ የሚሰሩ
የቡድን ሚናዎች እና ፈቃዶች
ሰራተኞችን ይጋብዙ እና ለእያንዳንዳቸው በትዕዛዞች፣ ቻቶች፣ ወይም እቃዎች ላይ ብቻ የተገደበ ፈቃድ ይስጡ።
የእቃ አማራጮች
ሳይዝ፣ ቀለም እና ሌሎች አማራጮች ሲኖሩ የየራሳቸው የዋጋ ማስተካከያ አላቸው።
የክምችት እና ብዛት ቁጥጥር
በእያንዳንዱ እቃ ላይ ያለዎትን ክምችት ይከታተሉ ወይም መኖር አለመኖሩን ያመልክቱ።
የደንበኞች አስተያየት መቀበያ
ገዢዎች ያላቸውን ተሞክሮ ደረጃ ይሰጣሉ፤ እርስዎ ደግሞ በአንድ ቦታ ሆነው ያስተዳድሩታል።
የሱቅዎ ገጽታ
የከቨር ፎቶ፣ የስራ ሰዓታት፣ የማህበራዊ ሚዲያ ሊንኮች እና የካርታ አቅጣጫ።
የተመረጡ እቃዎች ማሳያ
ገዢዎች ሱቅዎን ሲከፍቱ መጀመሪያ የሚቀበሏቸውን የተመረጡ እቃዎች ያዘጋጁ።
የተመራ ማብራሪያ
አዲስ ሱቆችን እስከ መጀመሪያ ሽያጫቸው ድረስ የሚመራ የማዋቀሪያ ዝርዝር።
ሙሉ የኦዲት መዝገብ
እያንዳንዱ ድርጊት የተፈጸመበት ጊዜ እና የፈጸመው ሰው በሱቅዎ ይመዘገባል።
ወደ መጀመሪያ ሽያጭዎ የሚያደርሱ አራት ደረጃዎች
ቦቱን ያነጋግሩ
@ShegaShop_Bot ን ይክፈቱ እና Create My Shop የሚለውን ይጫኑ — አጭር የማዋቀሪያ ፎርም ልክ ቴሌግራም ውስጥ ይከፈታል።
ፎርሙን ይሙሉ
ፎርሙ የሱቅዎን ስም ማውጣት እና የራስዎን ቦት እና ቻናል ማገናኘት ደረጃ በደረጃ ይመራዎታል። ከዚያ እቃዎችን ከነ ፎቶዎቻቸው ወይም አጭር ቪዲዮ ጋር ያስገቡ።
ፖስት ያድርጉ እና ይተዋወቁ
ወደ ቻናልዎ ፖስት ያድርጉ ወይም yourshop.shegashop.com የሚለውን ሊንክ ያጋሩ። ገዢዎች እቃዎችን ይቃኛሉ፣ ያወሩዎታል።
ትዕዛዝ ያድሱ እና ክፍያ ይቀበሉ
የትዕዛዙን ሁኔታ እስከ ርክክብ ድረስ ይከታተሉ፣ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ዝውውር ክፍያ ይቀበሉ — የባንክ ክፍያዎችም በራሳቸው ይረጋገጣሉ።
ትክክለኛው የዕድገት ጣሪያ የት ላይ ነው?
| ተግባር | የተለመደው የቴሌግራም ቻናል | ተራ የሱቅ መገንቢያ | ሸጋ ሾፕ |
|---|---|---|---|
| ለመጎብኘት ምቹ ሱቅ — መፈለጊያ እና ዘንቢል | የለም | አለ | አለ |
| ከእቃው ጋር የተገናኘ ከሰው-ወደ-ሰው ቻት | በእጅ የሚጻፍ የውስጥ መስመር | የለም | አለ |
| የትዕዛዝ ሁኔታ ክትትል | የለም | አለ | አለ |
| የባንክ ዝውውር ራስ-ሰር ማረጋገጫ | የለም | የለም | አለ |
| መርሐግብር የተያዘላቸው የቻናል ፖስቶች | የለም | የለም | አለ |
| ቴሌግራም ውስጥ የሚሰራ | አለ | የለም | አለ |
| የራስዎ የድረ-ገጽ አድራሻ | የለም | አለ | አለ |
ሻጮች ምን ይላሉ?
“ቻናሌ ዝም ብሎ የፖስቶች ማሳያ ነበር። አሁን ግን ሰዎች ገብተው የሚጎበኙት እውነተኛ ሱቅ ሆኗል — ምን ትዕዛዞች እንዳሉም በቀላሉ አውቃለሁ።”
“ቻቱ በቀጥታ ከሚጠይቁት እቃ ጋር የተገናኘ ነው። 'ቆይ የትኛውን ነው?' የሚል ጥያቄ ቀርቷል።”
“የባንክ ዝውውሮችን ማረጋገጥ የጠዋት ሙሉ ስራዬ ነበር። አሁን ግን ቅጽበታዊ ሆኗል።”
ቀላል እና ግልጽ ዋጋ
Unlimited scale with every feature, under your own brand
- ያልተገደበ የእቃዎች ብዛት
- በቀን ያልተገደበ የቻናል ፖስቶች
- 10 የቡድን አባላት
- ከሰው-ወደ-ሰው የእቃ ቻት
- የትዕዛዝ አስተዳደር እና ክትትል
- የባንክ ዝውውር ራስ-ሰር ማረጋገጫ
- የክፍያ መለያዎች
- የእቃ አማራጮች
- ፖስት መርሐግብር ማስያዣ
- በራስዎ አድራሻ የሚሰራ የድረ-ገጽ ሱቅ
- የሱቅ መግቢያ ባነር
- የማስታወቂያ ባነር
- የመተማመኛ ምልክቶች
- የመገናኛ እና ማህበራዊ ሚዲያ ሊንኮች
- 12 የተመረጡ እቃዎች
- የገቢ ትንተና
- የደንበኞች አስተያየት መቀበያ
እያንዳንዱ እቅድ በየወሩ፣ በየሶስት ወሩ ወይም በየአመቱ ይከፈላል። የትኛውንም እቅድ በማንኛውም ጊዜ መቀየር ይችላሉ።
ለጥያቄዎችዎ የተሰጡ መልሶች
በቻናሌ ላይ ፖስት ከማድረግ በምን ይለያል?
ቻናልዎ ልክ እንዳለ ይቆያል — ነገር ግን ፖስት የሚያደርጉት እያንዳንዱ እቃ ገዢዎች ሊፈልጉት፣ ሊያጣሩት እና ዘንቢል ውስጥ ሊከቱት ወደሚችሉት እውነተኛ ሱቅ ይገባል። ከጀርባው ደግሞ ከሰው-ወደ-ሰው ቻት እና የትዕዛዝ ክትትል አለው። ቻናሉ የሱቁ ዋና በር ይሆናል እንጂ ራሱ ሱቁ አይሆንም።
ዌብሳይት ላይ መመዝገብ አለብኝ?
አያስፈልግም። ቴሌግራም ላይ @ShegaShop_Bot ን ያነጋግሩ እና Create My Shop የሚለውን ይጫኑ — አጭር የማዋቀሪያ ፎርም ልክ ቴሌግራም ውስጥ ይከፈታል፣ ሲጨርሱትም ሱቅዎ ተከፍቷል።
የባንክ ዝውውር በራሱ መረጋገጥ ካልቻለስ?
ዳሽቦርድዎ ላይ ስክሪንሾቱን በማየት እራስዎ እንዲያረጋግጡት ይደረጋል — ትዕዛዞችን ከማረጋገጥ በፍጹም አይታገዱም።
የቡድን አባላቴ እኔ የማየውን ሁሉ ማየት ይችላሉ?
አይችሉም — ለእያንዳንዱ የቡድን አባል እርስዎ የሚመድቡት የተወሰነ ፈቃድ (ለትዕዛዞች፣ ለቻቶች፣ ወይም ለእቃዎች) ይሰጣቸዋል።
የደንበኞች መረጃ ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ ነው?
አዎ። ማንነታቸው በቀጥታ ከቴሌግራም ነው የሚወሰደው — የይለፍ ቃላት የሉም፣ በሱቆች መካከል የሚጋራ መረጃም የለም።
ቻናልዎ ከጀርባው እውነተኛ ሱቅ ያስፈልገዋል።
ቦቱን ያነጋግሩ፣ አንድ አጭር ፎርም ይሙሉ፣ በደቂቃዎች ውስጥ ትዕዛዞችን መቀበል ይጀምሩ።